የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪዎችን ከእነአስተሳሰባቸው ቀብረን ኢትዮጵያን እናስቀጥላለን – አቶ ተመስገን ጥሩነህ

By Tibebu Kebede

August 25, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አሸባሪዎችን ከእነአስተሳሰባቸው ቀብረን ኢትዮጵያን እናስቀጥላለን ሲሉ ገለጹ።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እየመጠመጡን የሚዘልቁ መስሏቸው ከሆነ ተሳስተዋል ብለዋል።

“ከእኛው ወልጋዳ ባንዳዎች ጋር ሆነው የሚሰሯትን እያንዳንዷን ሴራም እናውቃለን” ነው ያሉት አቶ ተመስገን።

“ካልደፈረሰ አይጠራም፣ ካልጠራ አይጠጣም” የሚለውን የአበው አባባል የጠቀሱት አቶ ተመስገን፣ ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ክብራቸውንና ነፃነታቸን የተጎናፀፉት በጀግኖች መስዋዕትነት መሆኑን አመልክተዋል።

አክለውም ኢትዮጵያውያን በነፃነታቸው ላፍታም አይደራደሩም፤ የትኛውም ቦታ ቢሆን ጁንታው እና ተባባሪዎቹ የእጃቸውን ያገኛሉ ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!