Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኢትዮጵያ ከተሜነት ፈጣን እድገት እያሳየ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ከተሜነት ፈጣን እድገት እያሳየ  መሆኑን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም ከተሜነት እንደ ሀገር 5 ነጥብ 4 በመቶ የደረሰ ሲሆን÷ በደቡብ ክልል ደግሞ  7 በመቶ  መድረሱ ተመላክቷል፡፡

ከገጠር ወደ ከተማ በሚደረግ ፍልሰት ምክንያት በደቡብ ክልል እየገዘፈ የመጣው ፈጣን ከተሜነት ሊገታ የሚችል ባለመሆኑ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ፣ ሰላማዊና ጽዱ ማድረግ ይጠበቃልም ነው ያሉት፡፡

ከተሞችን ፅዱ፣ ጤናማና ሳቢ ለማድረግ ጠንካራ የማህበረሰብ ተሳትፎ መገንባትና የአሰራር ደንቦችን እንዲሁም  የህግ ማእቀፎችን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂኒየር አይሻ መሀመድ ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በበኩላቸው፥ ሀላፊነቱን ተረድቶ በአግባቡ የሚሰራ አመራር ያለበት ከተማ ህይወት አለው  ነው ያሉት፡፡

ለዚህም ከተሞችን አረንጓዴ፣ ጽዱና ለነዋሪው ምቹ ለማድረግ የአመራሩ ትጋትና ተነሳሽነት ወሳኝ በመሆኑ አመራሩ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘውም በከተሞች ነዋሪው ተረጋግቶ የሚኖርበት አመራሩም ተረጋግቶ የሚመራበትና የሚሰራበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓት የህግ ማእቅፍና መመሪያ ወደታች ወርዶ ተግባራዊ መሆን አለበት  ማለታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version