አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ምርጫ ባልተደረገባቸው ምርጫ ክልሎች ከሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ቀጣዩን የድምፅ መስጫ ቀን ይፋ አድርጓል።
ምርጫ ባልተደረገባቸው አካባቢዎች የሚኖረውን ቀጣይ የምርጫ ሂደት ከአካባቢዎቹ አጠቃላይ ሰላምና ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ዝርዝር መረጃ የተሰጠ ሲሆን፥ በቦርዱ ግምገማም ምርጫ ለማድረግ አመቺ ሁኔታ ያለባቸው ቦታዎችም ተለይተው ቀርበዋል።
ከውይይቱ በኋላም ቦርዱ የምርጫው ጊዜ ሰሌዳን ጨምሮ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ወስኗል።
በዚህም ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ምርጫ ባልተካሄደባቸው ምርጫ ክልሎች የድምጽ መስጫ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲሆን ወስኗል።
ከዚህ ባለፈም ድምፅ አሰጣጡ በሶማሌ ክልል፣ በሐረሪ ክልል እና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል እንደሚከናወን ጠቅሶ፥ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ህዝበ ውሳኔም በተመሳሳይ ቀን መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ይከናወናል ብሏል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!