የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽኑ በአማራና አፋር ክልሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስፈላጊው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

August 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ጥቃት ከአማራና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የብሔራዊ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር አይደሩስ ሀሰን ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ኮሚሽኑ በአሸባሪው ሕወሓት ጥቃት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ እየሰራ ነው።

ኮሚሽኑም በሁለቱም ክልሎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች የእለት ደራሽ ምግቦችን ጨምሮ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችንም በበቂ ሁኔታ እያቀረበ መሆኑን አስረድተዋል።

በተለይም በቅርቡ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስፈላጊው ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ ጎን ለጎንም ለአንድ ወር የሚበቃ የዕለት ደራሽ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የመጠቀሚያ ድጋፎችን ለተፈናቃዮች ቀደም ብሎ መድረሱንም አመላክተዋል።

በተመሳሳይ በአፋር ክልል በአሸባሪው ሕህወሓት ለተፈናቀሉ ዜጎች ኮምቦልቻና አዳማ ከሚገኘው የኮሚሽኑ ማዕከላዊ መጋዘን ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት ለተፈናቃዮች ከሚያቀርበው ምግብና ምግብ ነክ ድጋፎች በተጨማሪ መንግሥታዊ ያልሆኑ የረድኤት ተቋማትም ተመሳሳይ ድጋፍ እያደረጉ ነው ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!