አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታዋቂው ሙነሽድ መሐመድ አወል ሳላህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።
የቀብር ሥነ-ስርዓቱ ዛሬ ኮልፌ የሙስሊሞች መቃብር ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ተፈጽሟል።
በ1958 ዓ.ም በደሴ ከተማ የተወለደው መሐመድ አወል በዛው በሚገኙ መድረሳዎች መንፈሳዊ ትምህርቱን ተከታትሏል።
ታዋቂው የኪነ ጥበብ ሰው መሐመድ አወል ሳላህ ወደ ብሔራዊ ውትድርና ተቀላቅሎ ሀገሩን ማገልገሉን የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።
በ1980 ዓ.ም ደግሞ ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመሄድ ለሰባት ዓመታት ከቆየ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመልሶ መዚቃን ጨምሮ በተለያዩ ስራዎች ተሰማርቶ ቆይቷል።
በ2000 ዓ.ም ገደማ ሙዚቃን በመተው መንፈሳዊ ነሺዳዎችንና እንጉርጉሮዎችን መስራት የቻለው መሐመድ አወል ሶስት የነሺዳ ካሴቶችንና በርከት ያሉ በተለያዩ ጊዜ ያወጣቸው ስራዎች ለእምነቱ ተከታዮች አበርክቷል።
ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ኢብኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!