ዓለምአቀፋዊ ዜና

የኬንያ አየር መንገድ የቻይና በረራዎችን በጊዜያዊነት አገደ

By Tibebu Kebede

January 31, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኬንያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የቻይና በረራዎችን ለጊዜው ማገዱን አስታወቀ።

አየር መንገዱ ከኬንያ ቻይና እንዲሁም ከቻይና ኬንያ የሚደረጉ በረራዎችን ማገዱን አስታውቋል።

የእገዳውን የጊዜ ርዝመት ለመወሰን ከጤና እና ከውጭ ጉዳዮች ሚኒስትሮች ጋር ምክክር እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

ከቻይና ውጭ ወደ ታይላንድ ባንኮክ የሚያደርገው ጉዞ ግን ይቀጥላል ብሏል አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ።

ባለፈው ማክሰኞ ከቻይናዋ ውሃን ከተማ ወደ ኬንያ የተመለሰ ኬንያዊ ተማሪ ሆስፒታል ውስጥ በገለልተኛ ክፍል ምርመራ ሲደረግለት ቆይቷል።

በአፍሪካ በቫይረሱ ተይዘዋል በሚል የተጠረጠሩ ስድስት ሰዎች ቢገኙም በተደረገላቸው ምርመራ ሁሉም ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል።

ከቫይረሱ ስርጭት ጋር በተያያዘ የተወሰኑ ሃገራት ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎችን ማገዳቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ