ቢዝነስ

ወርቅ በሚወጣበት አካባቢ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ እንዲከፈት ይደረጋል ተባለ

By Amare Asrat

August 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወርቅ ምርትን ግብይት ህጋዊ መስመር እንዲይዝ የማስተካከያ ስራዎች እየተሠሩ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትሩ ኢንጅኒየር ታከለ ኡማና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በደቡብ፣ በሲዳማ፣ በጋምቤላና በቤንሻንጉል ከልሎች ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በዚህም የማዕድን ምርት በተለይም የወርቅ ምርትን ማሳደግ በሚቻልበት ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን÷ ወርቅ በሚወጣባቸው አካባቢዎች የንግድ ባንክ ቅርንጫፎችን ለመቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በውይይቱ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ህጋዊ ግብይት ለማካሄድ የሚያስችሉ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች እንዲከፈቱ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በወርቅ ግብይት ላይ የሚታዩ ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ስርአት የሚይዙበትን መንገድ ለማመቻቸት ይሰራልም ነው የተባለው፡፡

በቀጣይም በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ ጠንካራ ክትትል የሚደረግ ሲሆን÷ በአጠቃላይ የአዘዋዋሪዎች ፍቃድ ላይ ፍተሻ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

የፀጥታ ጉዳዮች አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው አቅጣጫ ከተቀመጠላቸው ውስጥ መሆኑን ከማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!