Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ዐይነ ሥውሩ በፈረስ ጉግስ ውድድር አሸናፊ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች 80ኛ ዓመት በዓል ቅድመ ዝግጅት ላይ በተደረገ የፈረስ ጉግስ ውድድር ዐይነ ሥውሩ አሸናፊ ሆነዋል።

ማየት ለሚችሉት ፈታኝ እና ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚጠይቀውና በከፍተኛ ፍጥነት በሚከናወነው የፈረስ ጉግስ ውድድር ላይ ዐይነ ሥውሩ ተወዳዳሪ ከፉክክር አልፎ ማሸነፋቸው ልዩ ትኩረትን ስቧል።

በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፋግታ ለኮማ ወረዳ የሚገኙት አቶ አዲስ ሰውነት ያላቸው ተሰጥኦ እንግዳ እና ትኩረትን የሳበ ሆኗል።

አቶ አዲስ የዐይን ብርሃናቸውን ከ8 ዓመታቸው ጀምሮ ያጡ ሲሆን፥ ከፍተኛ የእችላለሁ ስሜት ያላቸውና ይህንንም በተግባር ያሳዩ መሆኑ ተገልጿል።

ለ80ኛ ዓመት የሰባት ቤት የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ክብረ በዓል ቅድመ ዝግጅት ላይ በተደረገ ውድድርም በፈረስ ጉግስ አሸናፊ ሆነዋል።

አሸናፊው ሁሉንም ነገር ወደ ፊት እንጅ ወደ ኋላ አልልም፤ እወድቃለሁ ብየም ባለመስጋቴም ውድድሩን ማሸነፍ ችያለሁ ብለዋል።

መረጃው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ነው፤

Exit mobile version