አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ለመስጠት ኪነ ጥበብ ለሀገራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል የኪነ ጥበብ መድረክ አዘጋጅቷል።
በመድረኩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የመከላከያ ሠራዊት አባላት በየደረጃው ያሉ የፀጥታ አካላት እና የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ኪነ ጥበብ የህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ያለው ከመሆኑም በላይ ለሀገር ሉአላዊነት ክብር ለቆመው ለመከላከያ ሠራዊት ኪነ ጥበብ የሞራል ስንቁ መሆኑን ከንቲባው ተናግረዋል።
ስለሆነም ሠራዊቱን ሊያጀግኑ የሚችሉ መሠል የኪነጥበብ መድረኮች ሊጠናከሩ እንደሚገባም አንስተዋል።
በመርሀ ግብሩ የሀገር ፍቅር ስሜትን ያዘሉ መነቃቃትን የሚፈጥሩ ስነ ፁሁፎች፣ ሙዚቃዎች ድራማዎች መነባንቦች በአስተዳደሩ በሚገኙ የኪነጥበብ ባለሙያዎች አቀርበዋል ።
የዝግጅቱ ታዳሚዎች በበኩላቸው እንዲህ አይነት መድረኮችና ድጋፎች ከምንም በላይ ወኔ ሠጥቷቸው ትግሉን ከጫፍ ለማድረስ እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።
በቲያ ኑሬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!