አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን እና በቦረና አሸባሪው ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
በሰልፎቹ ላይ የጥፋትን ቡድኑን ድርጊቶች የሚኮንኑ መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡
የአሸባሪዎቹ ሸኔ እና የህወሓት ጥምረት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተደረገ ስምምነት በመሆኑ እድሜያቸውን ለማሳጠር ከመከላከያ ጎን እንቆማለን ብለዋል ሰልፈኞቹ፡፡
የምዕራብ አርሲ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብድረሃማን ገመዳ በኦሮሞ ታጋዮች አጥንት እና ደም ላይ ቆሞ ከህወሓት ጋር በይፋ የጀመረው ጥምረት ሸኔ የኦሮሞ ጠላት መሆኑን ያሳያል ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያኖች ሁለቱን አሸባሪዎች እድሜያቸውን ለማሳጠር ይበልጥ ተሳትፏቸውን ሊያጠናክሩ ይገባልም ብለዋል ሰልፈኞቹ።
በተመሳሳይ በቦረና ዞን ጎመሌ ወረዳ ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄዷል፡፡
በአጥንት እና በደም የቆመችውን ሀገር በአሸባሪዎቹ ሸኔ እና ህወሓት በፍጹም አትፈርስም ብለዋል የሰልፉ ተሳታፊዎች፡፡
ሀገርን ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ የትኛውም ሀይል ፊት ቆመን እንታገላለንም ነው ያሉት ባስተላለፉት መልዕክት።
የጎመሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ይሳቅ ጠቾ ሰልፍ የወጡትን የህብረተሰብ ክፍሎች በማመስገን፥ የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በቢቂላ ቱፋ ፤ ተጨማሪ መረጃ ከኦቢ ኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!