አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲው ለሁለተኛ ጊዜ በመደበኛ መርኃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 875 ተማሪዎችን አስመረቀ።
የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀጃው ደማሙ “ተመራቂ ተማሪዎች በልዩ ልዩ ችግሮች ሳትበገሩ ለምረቃ ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።
ተመራቂዎቹ ባለፉት ዓመታት ያካበቱትን እውቀትና ክህሎት ጠንክረው በመሥራት ለሀገር እድገት እና ልማት ማዋል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከውስጥም ከውጭም እየተቀነባበረ ያለውን ሴራ ለማክሸፍ የተባበረ ክንድ አስፈላጊ መሆኑንም አንስተዋል።
በመሆኑም የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች ድርብ ሃላፊነት እንደሚጠብቃቸው ተናግረዋል።
ተመራቂዎች በቀጣይ የሕይወት ጉዟቸው ከመንግሥት ሥራ ጠባቂነት ወጥተው የራሳቸውን የሥራ እድል መፍጠር ይገባቸዋል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!