አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ 230 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
የሀገርን ህልውና ለማስቀጠል ደም እና አጥንቱን እየገበረ ላለው ሰራዊት ደጀን በመሆን የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን 16 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርገዋል።
ከዚህ ባለፈም ከተቋማቱ የተለያዩ ወጪዎች ተቀንሶ 213 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በድምሩ 229 ነጥብ 9 ሚሊይን ብር ድጋፍ ተደርጎል።
ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪም አንድ ከፍተኛ አመራር ሁለት የቢሮ ሃላፊዎች እና አምስት ሾፌሮች በግንባር በመገኘት ድጋፍ እየሰጡ ነው ተብሏል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለጹን ኢብኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!