አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የሚሌ ከተማ ነዋሪዎች በህወሓት የሽብር ቡድን በጋሊ ኮማ ንፁሀን ላይ የደረሰውን የዘር ጭፍጨፋ የሚያወግዝ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።
በሰልፉ የሽብር ቡድኑ ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፍረስ እያደረገ ያለው መፍጨርጨር እንደማይሳካ የአፋር ህዝብ በአንድነት የሽብር ቡድኑን ለማጥፋት እንደሚሰራ ተገልጿል።
በህፃናትና ሴቶች ላይ በደረሰው አሳዛኝ እልቂትም አሸባሪው ህወሓት በዘር ማጥፋት ወንጀል ይጠየቅ የሚሉ መፈክሮች መስተጋባታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!