አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸና ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው ብረት መያዙን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።
ብረቱ በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደ ዘመቻ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ እየሱስ ገዳምና ጦር ኃይሎች ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኙ ሁለት ስፍራዎች ላይ ተከማችቶ የነበረና ከፍተኛ የዋጋ ግምት ያለው መሆኑን አስታውቋል።
አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ቡድን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስና ሀገርን የማፍረስ እኩይ ተልዕኮውን ለማሳካት የተለያዩ የኢኮኖሚ ኣሻጥር መረቦችን ዘርግቶ ሲሰራ መቆየቱንን ኮሚሽኑ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ያስታወቀው።
በዚህ መሰረት ቀደም ሲል በተሊያዩ 17 ቦታዎች ተከማችቶ በህዝብ ጥቆማና በክትትል የደረሰበትን በብዙ ቢሊየን ብር የሚገመት ብረት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ ስለመሆኑም መግለጹ ይታወሳል፡፡
ሰሞኑን ደግሞ ብረት አከማችተው የተገኙና በህገ ወጥ ድርጊት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ይህ ውጤት የተገኘው በህብረተሰቡ ትብብር በመሆኑ መረጃውን ላደረሱ ግለሰቦች ምስጋነ አቅርቧል።
በቀጣይም መሰል ጉዳዮች ሲያጋጥሙት በነፃ የስልክ መስመሮች 987፡ 816፣ 991 እና በቢሮ ስልክ 0111110111 (አዲስ አበባ ፖሊስ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ስልክ ቁጥር 0115524077 እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ስልክ ቁጥሮች 0115309027፥- 0115309231 0115309077 መረጃውን በማድረስ እንዲተባበሩም ጥሪውን አቅርቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!