Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፌስቡክ የፊት ገጽታን  ለመለየት በሚጠቀምበት መሳሪያ ዙሪያ የነበረውን ውዝግብ እልባት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፌስቡክ የሰዎችን ምስል ለማጣራት እና ለመለየት የሚጠቀምበት መሳሪያ ጋር ተያይዞ ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የህግ ክርክር እልባት መስጠቱ ተገልጿል።

ፌስቡክ በፈረንጆቹ 2010 የሰዎችን የፊት ገጽታ መለያዎች መሣሪያን መጠቀም በፈረንጆቹ 2010 ላይ  የጀመረ ሲሆን፥ መሣሪያው የተጠቃሚውን ፊት ገጽታ በመቃኘት ስለ ደንበኛው ማንነት ሃሳቦችን የሚያቀርብ መሆኑ ተገልጿል።

ምንም እንኳን ተጠቃሚዎች እሱን የማጥፋት አማራጭ ቢኖራቸውም፣ በወቅቱ ቴክኖሎጂው አወዛጋቢ ሆኖ መገኘቱ ተጠቁሟል።

ተቃዋሚዎቹ የፊት ገጽታ መለያ መሣሪያው በኢሊኖስ ግዛትከወጣው የግላዊነት ህጎችን ይጥሳል ብለው የተከራከሩ ሲሆን ÷በግዛቱ ለሚገኙ ቡድኖችም 550 ሚሊየን ዶላር ይከፍላልም ተብሏል።

ጉዳዩ በፈረንጆቹ ከ2015 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ፥ስምምነቱም በየሩብ ዓመቱ ከሚገኝ ገቢ  መሆኑም ተመላክቷል።

ይህ የፊት ገጽታ እውቅናው  በፖሊስ እና በአደባባይ ቦታዎችጥቅም ላይ ሲውል  በጥልቀት ክትትል እንደሚደረግበትም ተገልጿል።

በፈረንጆቹ ታህሳስ ወር 2017ተጠቃሚዎች ይበልጥ በቀላሉ ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ እንዲችሉ ተደርጎ የተሰራ ሲሆን ÷በ 2019 ፌስቡክ ይበልጥ በግላዊነት ላይ ያተኮረ እንዲሆን አድርጎ  አዲሱ የመቆጣጠሪያ አካል አድርጎ መስራቱም ነው የተገለጸው።

የማህበራዊ አውታር መረቡ  ይህንን ጉዳይ ለማህበረሰባችን እና ለባለአክሲዮኖቻችን ጥቅም ስንል  ለመፍታት ወስነናል ሲል አስታውቋል፡፡

ይህ ማስተካከያ የሰዎችን መረጃ እና ግላዊነትን ለመጠበቅ  በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን ትልቁ  መሆኑን የኢንቨስትመንት ባንክ  ጃንስትር የሆኑት  ክርስቶፎር ሮዝባች ተናግረዋል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

Exit mobile version