አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በህብረተሰቡ ተነሳሽነት ኦነግ ሸኔን ለማውገዝ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እና ዞኖች በተደረገው ሰልፍ ለተሳተፉ ነዋሪዎች ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የክልሉ ህዝብ የኦነግ ሸኔን የጥፋት ተግባር እና የክፋት እሳቤ በመገንዘብ በቂ ዝግጅት በማድረግ ማውገዙ፥ የፖለቲካ ብስለቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳይ መሆኑን ተረድተናል ነው ያለው በመግለጫው፡፡
ከዚህ ባለፈም አካባቢውን ከጠላት ለመጠበቅ ያለውን ዝግጁነት የሚያሳይ እና የሚያረጋግጥ ነውም ብሏል፡፡
በመሆኑም የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና የመንግስት አደረጃጀቶች ለሰልፉ ስኬት ላበረከቱት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርቧል፡፡
ሌሎች ዞኖች እና የተማ አስተዳደሮችም በህብረተሰቡ አነሳሽነት በቀጣይ ቀናት ተመሳሳይ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን ለመረዳት መቻሉንም አንስቷል፡፡
ህብረተሰቡም በአንድ በኩል የኦነግ ሸኔን የጥፋት እና ክፋትን ድርጊትን ማጋለጥ፥ በሌላ በኩል በተሟላ መንገድ የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ መዘጋጀት እንዳለበትም አስታውሷል።
መግለጫው አክሎም የትግል መንገዱ ትክክል መስሏችሁ ኦነግ ሸኔን የተቀላቀላችሁ ወጣቶች በመጸጸት ወደ ህዝባችሁ መመለሳችሁ ጅግንነታችሁን ያሳያል ብሏል፡፡
ከኦነግ ሸኔ የጥፋት ቡድን ውስጥ በመሳተፍ ታሪካዊ ስህተት ከመስራት ለመታቀብ የወሰናችሁ ለህዝብ እና ለመንግስት እጃችሁን እንድትሰጡ ሲል መልዕክት አስተላልፏል፡፡
የሀገርን ሉአላዊነትን ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት የሚንቀሳቀስ የትኛውንም ሀይል ያለ ምህረት በተከታታይ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን እያሳሰብን፣ህዝቡ እያሳየ ያለውን የሞቀ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል መንግስት ጥሪ አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን