አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ወደስፍራው ያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደረገላቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው እለት ወደ ቱርክ ማቅናታቸው ይታወሳል።
በቱርክ ቆይታቸውም ከፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ጋር በሁለትዮሽና በጋራ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚምከሩ ይጠበቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!