Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል፡፡
 
ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በማታው መርሃ ግብር ያስተማራቸውን 5 ሺህ 789 ተማሪዎች በቅርቡ ያስመርቃል፡፡
 
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የተገኙት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ÷ሀገራችን ፈተናዎችን አልፋ ወደ ስኬት እየተጓዘች ባለችበት ወቅት የተመራቂ ተማሪዎች ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የኢትዮጵያን ውድቀት አሰፍስፈው የሚጠባበቁ ጠላቶች በተሳካ ሀገራዊ ምርጫና በሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ሽንፈት ተላብሰዋል ነው ያሉት፡፡
 
አሁን ላይ ለሀገሪቱ እድገትና ለውጥ መሰናክል የሆነውን የህወሓት ሽብር ቡድን በጋራ ማጥፋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
 
እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባዩ ይህ አጥፊ ቡድን ባለፉት ጊዜያት ሀገራችን በመከፋፈል የሀገር ተስፋ የነበሩ ተማሪዎችን እኩይ አላማ በመጫን ሀገር ሲያተራምስ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
 
ዩኒቨርሲቲው ለመከላከያ ሰራዊት የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን የገለጹት ፕሮፌር ታከለ ÷ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችም የወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ተመራቂ ተማሪዎች እንደማንኛውም ማህበረሰብ ሀገር በማዳን ተግባር ላይ ሊሰማሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
 
በዛሬው ዕለት በተመራቂ ተማሪዎች የተተከለው ችግኝም ለሀገሪቱ ሰላም በዱር በገደሉ እየተዋደቁ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት መታሰቢያ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
 
ዩኒቨርሲቲው ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 500 ሺህ ችግኝ አፍልቶ አሻራውን እያሳረፈ ይገኛል።
 
 
በመለሰ ታደለ
 
 
ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version