Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሴቶች ኮከስና የሴቶች ሊግ አባላት ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚሰለፉ ገለፁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስና የሴቶች ሊግ አባላት ሃገር የማዳን ጥሪውን በመቀበል ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንደሚሰለፉ አረጋገጡ።
የኮኮሱ ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባዬ ገዛኸኝ የተለያዩ ስንቅና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ወደ ግንባር ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በዝግጅቱ ቆሎ፣ በሶ ፣ ደረቅ እንጀራ፣ ኩኪስ እና ለሴት መከላከያ ሰራዊት አባላት የሚውል የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስም ከመንግስትና ከግል ድርጅቶች መሰብሰቡንም ተናግረዋል፡፡
የሴቶች ኮከስና የሴቶች ሊግ አባላት ከዚህ ቀደም ሀገርን ለማዳን በግንባር ላይ ላለው የመከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version