አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርባ ምንጭ ከተማ ከ35 ኩንታል በላይ አደንዛዥ ዕፅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
አደንዛዥ ዕጹ በኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ሲዘዋወር መያዙን የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዳንኤል አረጋ ተናግረዋል።
የተያዘው አደንዛዥ ዕፅ በዛሬው እለት በሚመለከተው አካል በተገቢው መንገድ ከከተማ ውጭ የሚወገድ መሆኑን ከአርባ ምንጭ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አደንዛዥ እጾች በህብረተሰብ ጤና እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሁም በወጣቱ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ መሰል ድርጊቶችን በመጠቆም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።