አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሀት ቡድንን የሚቃወምና የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ስነ ስርዓት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሄደ።
ከጠዋት ጀምሮ በማስ እስፖርት እንቅስቃሴ በማድረግና በማስ እስፖርት ላይ በመገኘት ተቃውሞአቸውን አቅርበዋል
የሲዳማ ክልል ህዝብ ከመከላከያው ጎን መሆኑንም በተለያዩ መንገዶች የገለፀ ሲሆን በርካታ አካላትም በስነ ስርዓቱ ላይ በመገኘት ድጋፋቸውን አሳይተዋል ።
የክልሉ እስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሬው አሬራ በውስጥ የህውሓት ቅጥረኞችና የውጭ ሀይሎች ሀገሪቱ ላይ እያሳደሩ ያለው ጫና በግልጽ የሚታይ መሆኑን በመግለፅ ሁላችንም በአንድነት በመሆን ልናስቆማቸው ይገባል ብለዋል።
የክልሉ ባህል ቱሪዝምና እስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጀጎ አገኘው በበኩላቸው ቀድሞም ቢሆን ሀገርን የመጠበቅ ጀግንነት ያላቸው ዜጎች መኖሪያ ሀገር መሆኗንና ይም ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረው ክልሉም ግዳጁን በሚገባ እየተወጣ ይገኛል ሲሉ ገልፀው፥ሁሉችንም የሀገራችን ሰላም መጠብቅ አለብን ነው ያሉት።
የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከፍ አንዳትልና እንድታንስ ሲሰራ የነበረው ህወሀት ዳግም ሀገሪቱን ዝቅ ለማድረግ እየሰራች የምትገኝ በመሆኑ በጋራ በመቆም ልናስቆማቸው ይገባል ብለዋል።
ለሀገራችን የሚጠበቅብንን ሁሉ ማድረግ አለብን ብለዋል።
የተሻለች ሀገር እንድትሆንና የፈለግነው ደረጃ ላይ ለመድረስ ሀገርን መጠበቅ አለብን ያሉ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም እያበረከተ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የሲዳማ ክልልና የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች የክልሉ ልዩ ሀይልና የሰፖርት ማህበረሰብ በስነ ስርዓቱ ላይ ተሳትፈዋል።
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!