ህወሓት ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት ነው
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህወሓት የሽብር ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንትና አካባቢው፤ በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ፣ መርሳና አካባቢው፤ እንዲሁም በዋግህምራ ዞን ሰቆጣና አካባቢው እየተሰወደበት ባለው ወታደራዊ እርምጃ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡
የፅህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሽብር ቡድኑ ትላልቅ አዋጊዎች መገደላቸውን እና በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎችም መማረካቸውን ገልፀዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ንብረቶችም መዘረፋቸውን ነው የገለፁት፡፡
በዚህም የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሻቀቡን ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት፡፡
የተላለፈውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ህብረተሰቡ የሽብር ቡድኑን ግብዓተ መሬት ለማፋጠን ያሳየው ተነሳሽነትና ርብርብ የሚደነቅ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ ወጣቱ ተደራጅቶ አካባቢውን በንቃት መከታተል እና ከሽብር ቡድኑ ሰርጎ ገቦች መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የህልውና ዘመቻውን በገንዘብና አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!