አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ነዋሪዎች ከ1 ሚለየን ብር በላይ ግምት ያላቸው መድሀኒቶችን ለመከላከያ ድጋፍ አደረጉ።
ክፍለ ከተማው ከዚህ በፊት በመጀመሪያው ዙር ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን÷ አሁንም ለሁለተኛ ዙር የተለያዩ መድሀኒቶችን ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የክፍለ ከተማው አመራሮች የተናገሩት፡፡
የትኛውም ገንዘብ እና ቁስቁስ ህይወትን መግዛት አይችልም እና ይህ ለክንደ ብርቱው ሰራዊታችን ቢያንስበት እንጅ አይበዛበትም ነው ያሉት፡፡
በመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ መድሀኒት ህክምና መገልገያዎች አቅርቦት ሀላፊ ብርጋዴል ጄኔራል የሽመቤት ዘውዱ፣ ነዋሪዎቹ በ1 ሚለየን 558 ሺ 815 ብር የተገዙ የተለያያዩ መድሀኒቶችን በመግዛት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!