Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ህዝባዊ አደረጃጀቶች ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር የከተማቸውን ሰላምና ደህንነት እየጠበቁ ነው – የደሴ ከተማ ከንቲባ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝባዊ አደረጃጀቶች ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር የከተማቸውን ሰላምና ደህንነት እየጠበቁ መሆኑን የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል ተናገሩ።

በከተማዋ ከዚህ ቀደም መሰረታዊ ስልጠና ወስደው ወደስራ ከገቡ ወጣቶች በተጨማሪ አሁንም 1ሺህ ወጣቶች ዛሬ መቀላቀላቸውን ነው የገለፁት፡፡

የአሸባሪውን የህወሃት ቡድን ወረራ ተከትሎ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር 55 ሺህ ደርሷል ብለዋል፡፡

በዚህም ከተለያዩ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በ8 ማዕከላት ጊዜያዊ መጠለያዎችን በማዘጋጀት የድጋፍ ስራ እየተሰራም ነው ብለዋል፡፡

ከከተማዋ ፀጥታ በተጨማሪ ግንባር ላሉት ጀግኖች የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውን የተናገሩት ከንቲባው በከተማዋ ከ50 ሚሊየን በላይ ብር ድጋፍ መደረጉንም አስረድተዋል።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version