Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

10ኛው ዙር «ጉሚ በለል» ውይይት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ላይ አተኩሮ እየተካሄደ ነው

 

10ኛው ዙር «ጉሚ በለል» ውይይት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ላይ አተኩሮ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ሂደት የኦሮሞ ሚና ” በሚል 10ኛው ዙር «ጉሚ በለል» የውይይት መድረክ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በመካሄድ ላይ ነው።

የውይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት የታሪክ ምሁሩ ታቦር ዋሚ፤ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን ጠብቃ እንድትቆይ የኦሮሞ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

እነ አብዲሣ አጋ፣ ገረሱ ዱኪ፣ አብቹ የሰላሌው፣ ገበየው ጉርሙ እና ሌሎችም በመላ ኢትዮጵያ አገር ወዳድ ጀግኖች ጋር በመሆን ኢትዮጵያ በውጪ ወራሪ እንዳትያዝና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ እንድትኖር ታላቅ ተጋድሎ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

በተለይ ጀግናው አብዲሣ አጋ፤ ኢትዮጵያ በጣሊያን ቀኝ ግዛት እንዳትያዝ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ትልቅ ጀግንነት መፈፀሙን አስታውሰዋል።

በእነዚህ ጀግኖች ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ኢትዮጵያ አሁንም የኦሮሞ ህዝብ ጠብቆ የማቆየት አደራ አለበት ብለዋል።

የኦሮሞ ሀዝብ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ እንድትኖር የራሱን አስተዋጽኦ ማድረግ ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

የታሪክ ምሁር ታቦር ዋሚ በቅርብ ጊዜ ” የኦሮሞ ማንነት እና ታሪኩ ” የሚል መጽሐፍ አስመርቀው ለንባብ ማብቃቸው ይታወቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version