አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽብርተኛው የህወሀት ቡድን የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በሰመራ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የመዝናኛ ፕሮግራም በማዘጋጀት ህዝቡ እንዳቅሙ በ1000 በ500 እና በ100 ብር የሚሸጡ ትኬቶችን ገዝቶ እንዲገባ በማድረግ ነው ለመሰብሰብ የታቀደው።
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ኮሚቴ አባል የሆነው መሀመድ አህመድ እንደገለጸው ከትኬት ሽያጩ እስከ 1ነጥብ5 ሚልየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል።
ህዝቡ ከሚሊሻው እና ከልዩ ሀይሉ እንዲሁም ከሰራዊቱ ጎን በመሆን ሽብርተኛውን የህወሓት ቡድን ለመዋጋት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው ተብሏል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ አዝናኝ እና ቀስቃሽ የጥበብ ስራዎች ቀርበዋል።
በመርሃ ግብሩ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን የመዝናኛ እና የጥበብ ሥራዎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
በጥበበሥላሴ ጀንበሩና አወል አበራ