አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 3ተኛ ዙር 8ተኛ የስራ ዘመን 13ተኛ መደበኛ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ፡፡
ጉባኤው በቆይታው 2013 በጀት የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ይወያያል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም 12ተኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ እና የ2014 በጀት አመት ቋሚ ዕቅድ በጀት ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!