አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ፋውንዴሽን “ደማችን ለሰራዊታችን” በሚል መሪ ቃል የክፍሉ የሰራዊት አባላት እና ሲቪል ሰራተኞች ደም ለገሱ።
የደም ልገሳው ዓላማ አሸባሪው ህውሃት በመከላከያ ባደረሰው ክህደት ሰራዊቱ ሃገርን ለማዳን በሚያደርገው ተጋድሎ ደም በመለገስ ከህልፈት ለመታደግ ነው።
አባላቱ ፣ ደም የምንሰጠው ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ያደረግነው ተግባር ለሰራዊታችን ምንም ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
ከሰራዊታችን ጎን በመሰለፍ በማንኛውም ሁኔታ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ደም የለገሱ ሲቪል ሰራተኞች መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!