ፋና ስብስብ

የ11 ዓመቷ ታዳጊ መተጣጠፍ የሚጠይቀውን የዮጋ እንቅስቃሴ ደጋግሞ በመከወን ክብረ ወሰን አስመዝግባለች

By Tibebu Kebede

January 30, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የ11 ዓመቷ ህንዳዊት ታዳጊ በአንድ ደቂቃ ውስጥ መተጣጠፍ የሚጠይቀውን የዮጋ እንቅስቃሴ ደጋግሞ በመከወን አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።

ታዳጊዋ ሪያ ፓላዲያ በአንድ ደቂቃ ውስጥ 21 ጊዜ የዮጋ እንቅስቃሴውን ሰርታለች።

ይህ የዮጋ እንቅስቃሴ እጅንም ሆነ እግርን ሳይጠቀሙ ጭንቅላትን ወደ ኋላ በመዘቅዘቅና በጀርባ ወደ መሬት ወርዶ መነሳትን የሚጠይቅ ድግግሞሽ ነው።

የሰውነት የመተጣጠፍ ችሎታን ከቅልጥፍና ጋር የሚጠይቀው ይህ እንቅስቃሴ አዳጋችና አስቸጋሪም ነው።

ታዳጊዋም ይህን እንቅስቃሴ በሚያስደንቅ ቅልጥፍና በ60 ሰከንዶች ውስጥ 21 ጊዜ አጋዥ ነገር ሳትጠቀም መከወን ችላለች።

በዚህም ከዚህ ቀደም ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ስሟን በህንድ ወርቃማ ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ አስፍራለች።

ከዚህ ቀደም ተይዞ የነበረው ክብረ ወሰን በአንድ ደቂቃ 17 ጊዜ ሲሆን ይህም በ8 አመት ታዳጊ ህጻን የተከወነ ነበር።

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል