አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር አና ፋሩ እና በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር
ኑዝሃ ዓለዊ መሃመዲ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም አምባሳደሮቹ ስለ ኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና እድሎች ገለፃ የተደረገላቸው ሲሆን÷ በቀጣይ ሁለቱ ሀገራት ኢንቨስተሮቻቸውን ወደ ሀገራችን በመላክ የኢንቨስትመንት ፍሰቱን መጨመር ስለሚቻልባቸው መንገዶች መክረዋል፡፡
በተጨማሪም÷ ኢንቨስትመንቱን በጋራ የማስተዋወቅ ስራ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ኮምሽነር ለሊሴ ነሜ የኮምሽኑን አዲስ የህንፃ ገፅታ ለአምባሳደሮቹ እንዳስጎበኟቸውም ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!