አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ በቆየባቸው ጊዜያት አሸባሪው የህወሃት ቡድን የተለያዩ የመብት ጥሰቶችንና ወንጀሎችን ሲፈፅም እንደቆየ የአይን እማኞች አጋለጡ።
ከአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው በደሴ የተጠለሉ ዜጎች እንዳሉት አሸባሪ ቡድኑ የመንግስትና የመከላከያ ደጋፊ ናችሁ በሚል በአላማጣ ከተማ የተለያዩ በደሎችን አድርሷል።
ከበደሎች መካከል ንፁሃንን ከነቤታቸው እንዲቃጠሉ ማድረግ፣ ግድያ፣ በተሽከርካሪ በአደባባይ መጎተትና ሌሎች አሰቃቂ ጥቃቶች እንደተፈፀሙ የዓይን እማኞች ገልፀዋል።
አንዲት አራስ የመንግስት ደጋፊ ነበርሽ በሚል ቤቷ ውስጥ እንዳለች ቤቷ እላይዋ ላይ እንዲነድ ማድረጉንም አክለዋል።
የዓይን እማኞቹ አክለውም አሸባሪው ህወሃት ንፁሃን ዜጎችን አሰገድዶ ወደ ግምባር በመውሰድ ሲቪሎችን እንደጋሻ የጥይት ማብረጃ የማድረግ አካሄድን ተከትሏል።
በዚህም በማንነታቸው ምክንያት በርካታ ወጣቶች በሽብር ቡድኑ ተገድለዋል።
ኢትዮጵያዊያን እያካሄዱት የሚገኘው የህልውና ዘመቻ ለተጎጂዎች ፍትህን የሚያስገኝ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!