አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍቅር ይሻለኛል እና ሌሎች አጫጭር ታሪኮች የተሰኘው ልብወለድ መጽሐፍ ተመርቋል፡፡
የፋና ብሮድካቲንግ ኮርፖሬት ባልደረባ በሆነው አብርሃም ፈቀደ የተጻፈው ይህ የልብ ወለድ መጽሐፍ በ172 ገጾች የተዋቀረ እና 14 የተለያዩ ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡
በመጽሐፍ ምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን ÷በመድረኩ ገጣሚያንና ደራሲያን ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡
እንዲሁም ከመጽሐፉ ውስጥ የተቀነጨቡ ታሪኮች ለታዳሚያን ቀርበዋል፡፡
ከመጽሐፉ ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ታሪኮች እውነተኛ ታሪክን መነሻ አድርገው የተጻፉ መሆናቸውን ደራሲው ገልጿል፡፡
ከነዚህም መካከል በአድዋ የክተት አዋጅ ላይ ተመስርቶ በሐዘንህ እርዳኝ፣ እንዲሁም በሁለተኛው የጣልያን ወረራ ወቅት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በብሪታኒያ ባዝ ከተማ በስደት በሚኖሩበት ወቅት ያጋጠማቸውን በምናብ ያስቃኛል፡፡
በተጨማሪም ‘’ሎንግ ዎክ ቱ ፍሪደም’’ በተሰኘው በነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ መጽሐፍ ላይ የሚገኝ አንድ ዓረፍተ ነገር ላይ ተመስርቶ ማንዴላና ነጯ እመቤት የተሰኘ አጭር የልበወለድ ታሪክ ማካተቱንም ነው የተናገረው፡፡
በፌቨን ቢሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!