Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የህውሀት ጁንታ በግዳጅ ወደ ጦርነት በአፋር ያሰለፋቸው ህፃናትና ወጣቶች እጅ መሰጠታቸውን ቀጥለዋል

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) – በቀላሉ አዲስ አበባ እንገባለን: አፋር ሰመራ ለመድረሰ 77 ኪሎ ሜትር ነው የቀረን ብለው ዋሽተውን ሶስት ቀን አሰልጥነውን አሰገድደው ወደ ጦርነት ማገዱን ሲሉ የህውሀት ጁንታ በአፋር ፈንቲ ረሱ ግንባር ያሰለፋቸው ህፃናትና ወጣቶች ገለጹ፡፡

እንደ አፋር ክልል መገናኛ ኤጀንሲ ገለጻ ህውሀት በአፋር ግንባር ያሰለፋቸው ህፃናትና ወጣቶች ከግንባር እየጠፉ እጅ መሰጠታቸውን ቀጥለዋል፡፡

“ይሄው እኛም ለአፋር ልዩ ሀይል እጃችንን ሰጥተን የቆሰልነውን አሳክመውን እነሱ ባሉት መንገድም ባይሆን አፋር ሰመራ እጃችንን በፍላጎታችን ሰጥተን ገብተናል,” ሲሉ ህፃናቶቹና ወጣቶቹ ተናገረዋል፡፡

“በጥሩ ሁኔታ ላይም እንገኛለን:: ለትግራይ ወጣቶች ወደ ጦርነት አትግቡ የገበችሁም ካላችሁ እጃችሁን በሰላም እንደኛ ሰጡ እንላለን,” በማለት ተናግረዋል ።

“ወደ ጦርነት እንድንገባ የሚቀሰቅሱን ነገር ሁሉ ውሸት ነው:: የራሳቸውን ልጆች ውጭ ሀገር እያሰተማሩ እኛን ትርጉም ለሌለው ጦርነት ህይወታችን እንዲያልፍ እያደረጉን ነው” ብለዋለ ።

ምንጭ:-የአፋር ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version