አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌደሬሽን በአርሲ ዞን በ4 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ያስገነባውን ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች አስመርቆ አስረከበ።
ፌደሬሽኑ ንብረቱ በሆነው በአሰላ ብቅል ፋብሪካ በኩል በቁሉምሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አስገንብቶ ያስረከበው አንድ ብሎክ ህንፃ 6 የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፃህፍት፣ የአስተዳደርና የመምህራን ማረፊያን ያካተተ ነው፡፡
የእነዚህ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ የቆየ ሲሆን የማስተካከያ ስራዎች ተከናውነው በአራት ወራት ተጠናቆ ለምርቀት መብቃቱ ተገልጿል።
የፌደሬሽኑ ምክትል ኃላፊ አቶ አለማየሁ ተሾመ ፌደሬሽኑ የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት በተለያየ መልኩ እያረጋገጠ መሆኑን ጠቅሰው፥ ከሚያገኘው ገቢ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን እያስገነባ መሆኑን ገልጸዋል።
በምረቃው ስነስርዓት ላይ የፈዴሬሽኑ አመራሮች ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዞኑ ሃላፊዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በኤርሚያስ ቦጋለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!