Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ባለስልጣኑ በ198 ሺህ ደንበኞች የሞባይል ስልኮች ላይ በተጫነ መተግበሪያ ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በ198 ሺህ ደንበኞች የሞባይል ስልኮች ላይ በተጫነ መተግበሪያ ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

አሰራሩ በመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ እና የመንግስት ተቋማት እና በሌሎች የውሃ አገልግሎቶች ላይ ተግባራዊ በመደረጉ ደንበኞች የሞባይል ስልኮች ላይ በተጫነ መተግበሪያ አማካኝነት ቆጣሪ ማንበብ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ይህም ግምታዊ አሞላልን ከማስቀረት ባለፈ ደንበኞች የውሃ ፍጆታቸውን በተጠቀሙበት ወር ለመክፈል የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ወር ጀምሮም በአራት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በሚስተናዱ 198 ሺህ 428 ደንበኞች ዘመናዊ የቆጣሪ ንባብ ስርዓት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

የክፍያ ስርዓቱ ደንበኞች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል በተዘረጉ የተለያዩ የክፍያ አማራጮች በመጠቀም የታህሳስ እና የጥር ወር የውሃ አገልግሎት ክፍያ መፈጸም የሚችሉ መሆኑንም ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version