አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ዛሬ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይሳተፋሉ፡፡
ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ ለግማሽ ፍፃሜ ያለፉት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር እና ለምለም ሀይሉ ለፍፃሜ ለማለፍ ይወዳደራሉ፡፡
በተጨማሪም 8:00 ሰዓት ላይ በሴቶች 3000 ሜትር መሰናክል የፍፃሜ ውድድር መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድምአገኝ ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ለማምጣት ጠንካራ ፋክክር እንደሚያደርጉ ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!