Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ያተኮረው የሀገራት እድገት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 27፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) ኮቪድ 19 ከተከሰተ ወዲህ አሜሪካ እና ቻይናን ጨምሮ የተለያዩ የአለም ሃገራት ፊታቸውን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚው እያዞሩ ነው፡፡
በዘርፉ በቅድሚያ ሚነሱት ቻይና እና አሜሪካም ፈጣን የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ መሆኑን የቻይና የመረጃና ኮሙኒኬሽን አካዳሚ ሪፖርት አመላክቷል፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት የሃገራቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ከፍ እያደረገ ሲሆን÷ ትኩረታቸውንም ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እያዞሩ እንደሆነ ይገለጻል፡፡
ይህም የሀገራቱ ኢኮኖሚ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የጎላ ተፅዕኖ ሳይደርስበት እንዲቀጥል አግዟል ነው የተባለው፡፡
በሪፖርቱ እንደተጠቆመው በፈረንጆቹ 2020 የ47 ሀገራት የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ 32 ነጥብ 6 ትሪሊየን ዶላር ደርሷል፡፡ ይህም በየዓመቱ በ3 በመቶ እድገት እያሳየ እንደሚቀጥል ነው የተመላከተው፡፡
ሪፖርቱ÷በፈረንጆቹ 2020 አሜሪካ በዲጂታል ኢኮኖሚዋ 13ነጥብ 6 ትሪሊየን ዶላር ማንቀሳቀስ እንደቻለች ሲያመላክት፣ ቻይና 5 ነጥብ 4 ትሪሊየን ዶላር፣ ጀርመን 2 ነጥብ 54 ትሪሊየን ዶላር፣ ጃፓን 2 ነጥብ 48 ትሪሊየን ዶላር እንዲሁም ዩናይትድ ኪንግደም 1 ነጥብ 79 ትሪሊየን ዶላር ማንቀሳቀሳቸው ነው የተገለፀው፡፡
አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ጀርመን 60 በመቶ የሚሆነውን ዓመታዊ ጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት በዲጂታል ኢኮኖሚው ሲመሩ÷ ቻይናም 40 በመቶ የሚሆነውን ጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት በዚሁ ዘርፍ ትከውናለች ተብሏል፡፡
ለቻይና የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት÷ ኢንዱስትሪት እና የ 5ኛው ትውልድ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላይ በትኩረት መሰራቱ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡
የአሜሪካ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት የተመዘገበው ደግሞ በቴክኖሎጂያዊ የፈጠራ ስራዎች ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የአውሮፓ ሀገራትም የዲጂታል ኢኮኖሚ ምርምርና አስተዳደር ላይ አተኩረው በመስራታቸው ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ÷ ሲጂቲ ኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version