አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አትሌት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር እና አትሌት ለምለም ኃይሉ በ1500 ሜትር ለግማሽ ፍጻሜ አልፈዋል።
በተካሄደው የቶኪዮ ኦሎምፒክ የሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ በሶስት የተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪ አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ሲያልፉ ድርቤ ወልተጂ ማጣሪያውን ማለፍ አልቻለችም።
አትሌት ፍሬወይኒ ገ/እግዚአብሄር በ4:04.12 እና አትሌት ለምለም ኃይሉ በ4:05.49 በተመሳሳይ ከየምድባቸው 5ኛ ደረጃን በመያዝ ቀጣዩን ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀሉ ሲሆን፥ ውድድራቸውን ረቡዕ እኩለ ቀን ላይ ያደርጋሉ።
በሌላኛው ምድብ ውድድሯን ያደረገችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ4:10.25 በሆነ ሰዓት 12ኛ ደረጃን በመያዟ ማጣሪያውን አለማለፏን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!