አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕቅድን ለማሳካት ተጨማሪ 20 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እየሰራ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ እቅዱን ለማሳካት ከአጋር ሀገራት የ10 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ያገኘ መሆኑን የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡
እቅዱን ለማሳካት ተጨማሪ 20 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ሚኒስቴሩ እየሰራ መሆኑን በመግለፅ ይህም በቅርቡ እንደሚጀመር ገልፀዋል፡፡
ግብር ከፋዮችም ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በታመኝነትና በወቅቱ የሚጠበቅባቸውን ግብር በመክፈል ግዴታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ቀሪውን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፕግሮራም ለማሰካት ተጨማሪ ገቢ ለመሰብሰብ የተዘጋጀውን እቅድ በቁርጠኝነት ማከናወን እንችላለን ብለዋል።