Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቦርዱ በቁጫ/ሰላም በር ምርጫ ክልል የተደረገውን የድጋሜ ቆጠራ ውጤት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በቁጫ/ሰላም በር ምርጫ ክልል የተደረገውን የድጋሜ ቆጠራ ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 19 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የማሳወቂያ ደብዳቤ፤ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ ተከትሎ በቁጫ/ሰላም በር ምርጫ ክልል ከመነሻው ጀምሮ ቅሬታና አቤቱታዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎቸ እየቀረቡ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡

ቦርዱ ሊከተሉ የሚችሉ ሥጋቶችን ለማስቀረት በማሰብ የድምፅ ማዳመር ሂደቱ እንዲቆምና ውሣኔ እስኪሰጥበት ድረስ ሠነዶቹን አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲደረግላቸው ማድረጉም ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ ሰኔ 27 ቀን 2013 ዓ.ም. አዲስ አበባ በሚገኘው ማዕከሉ የብዙኃን መገናኛ አካላትና የፓርቲ ተወካዮች በተገኙበት ያካሄደው እና በቦርዱ ይፋ የተደረገውን የድጋሜ ቆጠራ ውጤት ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡


ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version