አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዐቃቤ ህግ በእነ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ጀነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሳኤን ጨምሮ በ74 ሰዎች ላይ ክስ መሰረተ፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተዉ ተከሳሾች የፌዴራል መንግስትን በሀይል ለመለወጥ በማሰብ በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ጥቃት ለማድረስ የሚችል የትግራይ ማእከላዊ መንግስት ወታደራዊ ኮማንድ በማደራጀትና በመምራት በትግራይ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ላይ በሚገኙ የሰሜን እዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣በፌዴራል ፖሊስ እና በፌዴራል የመንግስት ተቋማት ላይ እንዲሁም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በተጨማሪም በኤርትራ ላይ ጥቃት በማድረሳቸዉ ነዉ፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በ 1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)(ለ)፣33፣35፣38 እና የሽብርን ወንጀል ለመከላከል ለመቆጣጠር በ2012 ዓ.ም የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀፅ 3(2) የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዉ በመገኘታቸዉ የሽብር ወንጀል ክስ መስርቶባቸዋል፡፡
ዐቃቤ ህግ ክስን ያስረዱልኛል ያላቸዉን ከ500 በላይ የሰዉ ምስክሮችን፣ ከ5ሺህ ገፅ በላይ የሆነ የሰነድ ማስረጃዎችን እንዲሁም የቴክኒክና የቪዲዮ ማሰረጃዎችን አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል፡፡
ክሱ የቀረበለት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ተኛ የፀረ ሽብር ወንጀል ችሎት በመዝገብ ቁጥር 272829 የሽብር መዝገቡ ተከፍቶ ጉዳዩን እየተመለከተዉ ይገኛል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!