Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከተማ አስተዳድሩ ከነዋሪዎች እና ባለሃብቶች ያሰባሰበውን የ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከከተማው ነዋሪዎች እና ባለሃብቶች ያሰባሰበውን የ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ድጋፍ ለመከላከያ ሰራዊት አስረክቧል፡፡
ድጋፉን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመከላከያ ሚነስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አስረክበዋል፡፡
“ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ!” በሚል መርህ የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የወሰኑ ወጣቶች የሽኝት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ወጣቶች ሀገርን በመከፋፋል እያሴረ የሚገኘው የሽብር ቡድን ህወሓት ለመደምሰስ መከላከያን ሰራዊትን ለመቀላቀል በመወሰናቸሁ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የትግራይ ወጣቶች የህወሓት እኩይ ተግባርን ከማጽፈጸም እራሳቸውን እንዲቆጥቡ እና የሽብር ቡድኑን ድርጊት እንዲያወግዙጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወጣቶች መከላከያን በመቀላቀል የሽብር ቡድኑን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ደምስሰው እንደሚመለሱ እምነታቸው መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
የጁንታውን የውክልና ጦርነት ለማምከን የትግራይ ህዝብ ልጆቹን በመምከር ከጁንታው ኃይል እንዲነጥል እና ከመላው ኢትዮጵዊ ጎን እንዲቆምም ጠይቀዋል፡፡
አባት አርበኞች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች ለዘማቾቹ የአገራቸውን አንድነት ለማስጠበቅ ያሳዩትን ቁርጠኝነት በማድነቅ መርቀውም ሸኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version