አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በጀት ዓመት ከ279 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ገለጹ፡፡
ሚኒስቴሩ 290 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የእቅዱን 96 ነጥብ 2 በመቶ ማሳከቱንም ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ እቅድ አፈጻጸሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ19 ነጥብ 6 በመቶ እድገት ወይም የ45 ቢሊየን ብር ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል፡፡
የእቅድ አፈጻጸሙ የኮሮና ወረርሽኝ እና የትግራይ ክልል ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች አካባቢዎች ላይ ያሉ ችግሮች ባሉበት የተገኘ በመሆኑ አበረታች ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!