ቢዝነስ

በበጀት አመቱ ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 62 ቢሊየን ዶላር ተገኝቷል

By Tibebu Kebede

July 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት አመቱ ከወጪ ንግድ 3 ነጥብ 62 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ገቢው ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች የተገኘ ሲሆን፥ በዋናነት ከግብርና ምርቶች እና ማዕድን ዘርፍ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የግብርና ምርቶች 2 ነጥብ 47 ቢሊየን ዶላር ገቢ በማስገኘት ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡

ከዚህ ባለፈም ከማምረቻው ዘርፍ 390 ሚሊየን ዶላር፣ ከማዕድን 668 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም ከአገልግሎት ዘርፍ 93 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል፡፡

ከምርት አንጻርም ቡና 25 በመቶ፣ ወርቅ 19 በመቶ እንዲሁም አበባ እና ሌሎች ምርቶች ደግሞ 13 በመቶ ድርሻ አላቸው ተብሏል፡፡

ገቢው ከ2012 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ19 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ነው የተገለጸው፡፡

አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ጃፓን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ሲንጋፖር፣ እስራኤል እና ቻይና ደግሞ የምርቶቹ መዳረሻዎች ናቸው፡፡

የወጪ ንግድ አፈጻጸሙ 88 በመቶ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በቆንጅት ዘውዴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!