Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአልባሳት ምርት ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቅረፍ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በአልባሳት ምርት ላይ የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለመቅረፍ እየተሰራ ነው፡፡
የልብስ ምርት ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ የማምረቻ ተቋማትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን የአግሮ-ፕሮሰሲንግና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገ/የሱስ ገልጸዋል፡፡
የንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶችን ለማበረታታትና ምርታማነቱን ለማሳደግ የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝም ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ የመጣውን የአልባሳት ዋጋ በዘላቂነት ለመቅረፍ አምራቾቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማህበረሰብ የሚያቀርቡበትን የግብይት ስርዓት ለመፍጠርም መታቀዱን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አንዳንድ ነጋዴዎችና አከፋፋዮች ምርቱን ከአምራቾቹ በዝቅተኛ ዋጋ ገዝተው በህገ-ወጥ መልኩ በማከማቸትና በተጋነነ ዋጋ በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት ደግሞ የጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራቾች ማህበር ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብይ ግደይ ናቸው፡፡
እንደ ምግብ ሸቀጦች ሁሉ የአልባሳት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በሰፊው ተደራሽ ለማድረግ የሚረዱ የግብይት ማዕከላት እንዲኖሩ በማድረግ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version