አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሜሪካ 453 ሺህ 600 ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑ ተገለጸ።
በአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ የሚደረገው ክትባት “ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን” የተባለው ክትባት ሲሆን የፊታችን ሰኞ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ርክክብ ይደረጋል ተብሏል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በተገኙበት ርክክቡ የሚከናወን እንደሆነም ታውቋል።
አሜሪካ በሚቀጥሉት ሳምንታት 25 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ለ49 የአፍሪካ አገራት ድጋፍ የምትለግስ መሆኑን “ጋቪ” በተሰኘ ዓለም አቀፍ ክትባት አቅራቢ ተቋም ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
በመጀመሪያው ዙር ድጋፍ አንድ ሚሊየን ዶዝ ክትባት ለቡርኪና ፋሶ፣ ለጂቡቲ እና ኢትዮጵያ ተደራሽ እንደሚሆንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!