Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአየር ፀባዩን ተከትሎ የአንበጣ መንጋ በተለያዩ ቦታዎች ተከስቷል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአየር ፀባዩን ተከትሎ የአንበጣ መንጋ በተለያዩ ቦታዎች መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሐምሌ ወር መግቢያ በሶማሌ ክልል÷ አሁን ላይ ደግሞ በምሥራቅ አማራ ደቡብ እና ሰሜን ወሎ እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ አካባቢ የአንበጣ መንጋው መከሰቱን በግብርና ሚኒስቴር የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ በላይነህ ንጉሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልፀዋል፡፡

አሁን ላይም መንጋው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት ክትትል እየተደረገ መሆኑን እና ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አንበጣ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ቀላል እንዳልሆነ በመረዳት አርሶ አደሩም ሆነ የክልል የግብርና ቢሮ የሥራ ሀላፊዎች በትኩረት ክትትል እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለመከላከል ስራውም ካለፈው ዓመት የተሻለ ዝግጅት መደረጉ የተገለፀ ሲሆን፥ የኬሚካል ርጭቱን እንደ ቦታው አቀማመጥ በተሽከርካሪ፣ በአውሮፕላን እንዲሁም በሄሊኮፕተር ለማካሄድ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡

በዚህ መሠረት ለኬሚካል ርጭት ሶስት አውሮፕላን እና አራት ሄሊኮፕተር መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው፥ በተጨማሪም ከ50 ሺህ ሊትር በላይ ኬሚካል መኖሩን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የዓለም ምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) እገዛ ለማድረግ ቃል መግባቱንም ነው የተናገሩት፡፡ በተጨማሪም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ መረጃ እየተለዋወጡ መሆኑን አስታውቀዋል።

በ ሲሳይ ጌትነት

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version