ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ ገብተዋል

By Tibebu Kebede

January 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ ገብተዋል።

አስመራ ሲደርሱም የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በአስመራ ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች ጋር እንደሚመክሩ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

መሪዎቹ በውይይታቸው በተለያዩ የሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትናንትናው እለት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ መግባታቸው ይታወሳል።