Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና በማርስ ላይ የምታካሂደውን ጥናት የፊታችን ሃምሌ ወር ትጀምራለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና በማርስ ላይ የምታካሂደውን የመጀመሪያ ሳይንሳዊ ጥናት የፊታችን ሃምሌ ወር እንደምትጀምር ይፋ አድርጋለች።

ጥናቱን የምታከናውነው ሳተላይት ሎንግ ማርች 5-ዋይ 4 በተሰኘ ሮኬት ወደ ህዋ እንደምትላክም የቻይና የጠፈር ምርምር ተቋም አስታውቋል።

ሮኬቱ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቅ የሚያሰችል አቅም እንዳለው በሙከራ ተረጋግጧልም ነው የተባለው።

ከሃይድሮጅን እና ኦክስጅን ጋዞች የተሰራ ሞተር ያለው ሮኬት በተያዘው ዓመት በርካታ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ያደርሳል ተብሎ ታምኖበታል።

ወደ ህዋ የምትላከው ሳተላይትም በማርስ ፕላኔት ዙሪያ በርካታ አዳዲስ ግኝቶች እና መረጃዎችን ለምርምር ተቋሙ ታደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ሺንዋ

Exit mobile version