ዓለምአቀፋዊ ዜና

በደቡብ አፍሪካ በተከሰተው ግጭት 72 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

By Meseret Awoke

July 14, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ግጭት 72 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ በተጠረጠሩበት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል የሀገሪቱ ፍርድ ቤት እንዲታሰሩ ውሳኔ ማሳለፉን በመቃወም በተነሳው ግጭት እና ሁከት የዜጎች ህይወት ሲያልፍ የንብረት መውደም እና ዝርፊያም እየተካሄደ ነው፡፡

ይህን ብጥብጥ ለማስቆም መንግስት እየወሰደ ባለው እርምጃ ብዙዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በሃገሪቱ እየተፈጸመ ያለውን የንጹሃን ዜጎች ግድያ እና የንብረት መውደም እንዲሁም ሁከት አውግዟል፡፡

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃማት በመግለጫቸው፥ በሃገሪቱ የህግ የበላይነት እንዲከበር እንዲሁም ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እና በፍጥነት ወደነበረበት እንዲመለስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!